fbpx
AMHARIC

በአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ጸደቁ

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ።

በመደበኛ ጉባዔው የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው የጸደቁ ሲሆን፥ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ6 ወራት ሪፖርት እና የ2009/2010 በጀት ዓመት የተከናወኑ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን አድምጦ በመገምገም አጽድቋል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ የክልሉ የ2010 በጀት ዓመት የ9 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሪፖርትንም አጽድቋል፡፡

እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን፣የኢንዱስትሪ ቢሮ መቋቋሚያ ቢሮ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልልመንግስት የቅማንት ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ ጸድቋል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የኔነህ ስመኝ ባለፉት ስድስት ወራት 320 ሺህ 650 የፍትሐቤርና የወንጀል ጉዳዮች ቀርበው ለ 271 ሺህ 631 መዝገቦች እልባት መሰጠቱንም ገልጸዋል፡፡

በፍርድ ቤቶች የቀጠሮ መዘገየቶች ላይ ጊዜ በማሳጠር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸው፥ በሰበር ሰሚ ችሎት አሁንም ረጅም ጊዜ እየወሰደ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት ካነሱዋቸው መካካል የተከራካሪዎች በህግ ባለሙያዎች ያለመታገዝ፣ የዳኞች የክህሎት ማነስ እንዲሁም ተከታታይ ስልጠናዎችን ያለመውሰድ የስነምግባር ችግር ተነስተዋል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ 2 ሺህ 819 ውሳኔ የተሰጠባቸው መዝገቦች ውስጥ በድንገተኛ ምርመራ 359 መዛግብት ዳግም የታዩ ሲሆን፥ በዚህ መነሻነትም በ49 ዳኞች ላይ ጉዳዮች እየተጣሩ እንደሚገኙም ተነስቷል፡፡

በፕሬዚዳንቱ የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ የህግና የፍትህ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በተሰሩ መልካም አፈጻጸሞችና ጉድለቶች ላይ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በሐሰተኛ ምስክሮች መቸገራቸውንም ገልጸዋል፤ እንዲሁም ሰው ገለዋል ተብለው ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የሟች በህይወት መገኘትንም አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ሐሰተኛ የህክምና ማስረጃ እና የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋለው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ለመታገልም የእምነት ተቋማት ማህበረሰቡ እና የተለያዩ ተቋማት በዚህ ጉዳይ ላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናይ የሚካሄድ ሲሆን፥ የተለያዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

 

ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram