fbpx
AMHARIC

ቀን ላይ እንቅልፍን የሚያዘወትሩ ሰዎች ለመርሳት በሸታ የተጋለጡናቸው- ጥናት

ቀን ላይ እንቅልፍ የሚያዘወትሩ እና ምሽት ላይ የተቆራረጠ እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ለመርሳት በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን አንድ ጥናት አመለከተ።

ተመራማሪዎቹ በተለይም እድሜያቸው ገፋ ያለ ጎልማሶች ላይ የተደረገው ጥናት ውጤት ላይ ቀን ላይ በሚያንቀላፉ ሰዎች አንጎል ላይ ለመርሳትበሸታ የሚያጋልጥ ፕሮቲን የሚያመነጭ ንጥረ ነገር በብዛት ታይቷል።

የመርሳት በሽታ /አልዛይመር/ “ቤታ አምሎይድ” የተሰኘ ፕሮቲን በአንጎል በሚሰበሰብበት ወቅት የሚከሰት የአዕምሮ በሽታ ነው።

ለዚህም ሰዎች በቂ እንቅልፍ በሚተኙበት ወቅት አንጎላቸው ፕሮቲኑን ማምረት የሚቀንስ ሲሆን፥ በተቃራኒው በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ከሆነ ደግሞ አንጎላቸው ፕሮቲኑን በብዛት እንደሚያመርት ተጠቁሟል።

ሆኖም ጥናቱ በዝቅተኛ እንቅልፍ ማግኘት እና የመርሳት በሽታን በሚያመጣው ነጥረ ነገር መካከል ስላለው ግንኙነት የሚያሳይ ግልፅ የጥናት ውጤት አለመኖሩን አመልክቷል።

በዚህ ጥናት 300 የሚሆኑ እድሜያቸው እስከ 70 ዓመት የሚደርስ አዛውንቶች የተሳተፉ ሲሆን፥ 22 በመቶ የሚሆኑት የቀን እንቅልፍ ያዘወትሩ እንደነበር ነው የተጠቆመው።

ተሳታፊዎችም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2016 ለሁለት ጊዜያት የአዕምሮ ምርመራ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በውጤቱ መሰረትም የቀን እንቅልፍ የሚያዘወትሩት ከማያዘወትሩት አንፃር ሁለቱም የአንጎል ክፍላቸው “ቤታ አምሎይድን” በብዛት ማምረቱ ተመልክቷል።

ምንጭ፦ webmd.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram