fbpx
AMHARIC

ሶፊ ሰላይዋ ሰው ሰራሽ አሳ

ባለ አንድ ዓይኗ ሮቦት አሳን ኤም አይ ቲ ኮምፒዩተር ሳይንስና ሰው ሰራሽ የማሰብያ ምርምር ማዕከል እውን ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ፈጣሪዎቿ ሶፊ ብለው የሰየሟት ይህች ሮቦት ዓሳ በጭራዎቿ ልክ እንደ ሌሎቹ አሳዎች መቅዘፍ ትችላለች።

የሶፊ ተልዕኮ ታዲያ እሷን መሳይ የሆኑ አሳዎችን ባህር ውስጥ ጠልቃ መሰለል ነው።

በዚህም የአሳዎቹ አኗኗር ሳይዛባ መኖሪያቸው ሳይረበሽ መረጃን የመሰብሰቢያ መልካም ዘዴ መሆኗን ፈጣሪዎቿ ይናገራሉ።

በባህር ውስጥ ወደ 15 ሜትር ጠልቃ እንደምትጓዝና ለ40 ደቂቃዎች እንደምትቆይ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

ሶፊን ከ10 ሜትር ርቀት ላይ በመሆን የሚቆጣጠራት ባለሙያም ተመድቦላታል።

ወደፊት እራሷን ችላ ውሳኔዎችን እንድትወስን በመስራት ላይ መሆናቸውን በፕሮጀክቱ እየተሳተፉ ያሉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ማዕከሉ ለሰባት ዓመታት ከውቅያኖስ በታች ያለውን ዓለም ፎቶ ሲያነሳና ሲቀርጽ እንደቆየ የገለጸ ሲሆን፥ ሶፊ ታዲያ የመጀመሪያዋ ሙከራ ነች ተብሏል።

ተመራማሪዎቹ ይህንን ፈጠራቸውን የውቅያኖስ ዓለምንና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመረዳት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆናቸው ነው ያነሱት።

ምንጭ፦ ምንጭ፦ ሲኤንኤን
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram