fbpx
AMHARIC

ሴኔጋል በዓለም ዋንጫው ያሸነፈች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች

21ኛው የአለም ዋንጫ በተለያዩ ሩሲያ ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በትላንትናው ዕለት በምድብ ስምንት ኮሎምቢያ ከጃፓን የተገናኙበት ጨዋታ የተካሄደ ሲሆን፥ ባልተጠበቀ ሁኔታ በጃፓን አሸናፊነት ተጠናቃል።

በዚህ ጨዋታ ኮሎምቢያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣት ቢሆንም በጃፓን 2ለ1 በመሆነ ውጤት መሸነፍ ግድ ብሏታል።

በጨዋታው ጃፓንን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ካጋዋ በ6ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት፤ ኦሳኮ ደግሞ በ73ኛው ደቂቃ ሲያሰቆጠሩ ኪውቴሮ ኮሎምቢያን ከመሸነፍ ያላዳነች ግብ በ39ኛው ደቂቃ አስቆጥሯለ።

አፍሪካን በውድድር መድረኩ ከወከሏት እና በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ደንቅ ብቃቱን ያሳየውን ሰይዶ ማኔን የያዘችው ሴኔጋል ፖላንድን 2ለ1 በሆነው ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

በጨዋታው ሴናግል አሸናፊ ማድረግ የቻሉትን ግቦች ፓላንዳዊው ሲዮኔክ በ37ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ እና ኒአንግ በ60ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።

ይህን ውጤት ተከትሎም ሴኔጋል በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የአለም ዋንጫ ውድድር አሸናፊ መሆን የቻለች ብቸኛ አፍሪካ ሀገር መሆኗን አረጋግጣለች።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram