fbpx
AMHARIC

ሳዑዲ አረቢያ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል 13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይፋ አደረገች

ሳዑዲ በጤና፣ ትምህርት፣ ስፖርት እና በመዝናኛው ዘርፍ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል የ13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይፋ አደረገች።

በፈረንጆቹ 2020 ተግባራዊ በማድረግ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችላት ሲሆን፥ ለ300 ሺህ ዜጎችም የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ለዚህ ፕሮግራም 13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ 60 በመቶውን መንግስት እና 40 በመቶው የግሉ ዘርፍ እንደሚሸፍን ተነግሯል።

የፕሮግራሙ ተግባራዊ መደረግ የግሉን ዘርፍ የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርገው አና የግሉን ዘርፍ በ2030 በሀገሪቱ ያለውን ሚና የተሻለ ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ ይረዳል ነው የተባለው።

በቅርብ ወራቶች የሳዑዲ መንግስት በሀገሪት የሙዚቃ ዝግጅቶች እና ሲኒማ ቤቶች ከረጅም ዓመታት በኋላ ስራ እንዲጀምሩ ማድሩ ይታወቃል።

ይህ እርምጃ ጥብቅ የእስላማዊ መንግስት አስተዳደር ስር ያለፈችው ሳዑዲ ለውጥ ላይ መሆኗን ያሳየ ነው ተብሏል።

በአሁኑ ወቅትም ሳዑዲ አረቢያ የዜጎቿን የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንድታሻሽል በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ሚድልኢስት ሞኒተር

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram