fbpx
AMHARIC

ሰበር ዜና – መቀመጫው በአሜሪካ ያደረገው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሊከፍት ነው

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የማኔጅመንት አባልና የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሞሐመድ አብዶሽ በመንገድ ላይ ነን ብለዋል፡፡

ላለፉት አራት አመታት መቀመጫውን አሜሪካ ሴንት ፖል ሚኔሶታ ላርፐንተር ጎዳና ላይ በማድረግ በሳተላይት የቴሌቪዥ ስርጭቱን እያከሄደ የሚገኘውና በጃዋር መሃመድ የሚመራው Oromia Media Network ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ መክፈት በሚቻልበት መንገድ ለመነጋገር ልዑካኑን ወደ አዲስ አበባ ልኳል።

የቴሌቪዥን ተቋሙ የማኔጅመንት አባልና የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ሞሃመድ አብዶሽ መሪነትና ሌላ አንድ የአመራር አባልን የያዘው ቡድን ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ኦኤምኤን የተለያዩ የሃገራችንን በተለይ የኦሮሚያን ወቅታዊ ጉዳዪች በኦሮምኛ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በሲዳምኛ፣ በእንግሊዝኛና በተለያዩ ቋንቋዎች ስርጭቱን የሚያስተላልፍ ሲሆን፤ በኔዘርላንድ፣ በለንደንና በካይሮ ተባባሪ ስቱዲዮዎችም አሉት።

የአሁኑ የቴሌቪዥን ተቋሙ አመራሮች ውሳኔ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦኤምኤን ስራ አስኪያጅ የሆነው ጃዋር መሃመድ ጋር በኦኤምኤን ላይም አብሮ ቀርቦ የነበረው ክስ መቋረጡን ተከትሎ ነው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram