fbpx
AMHARIC

‘ሰላም ጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን አዕምሮአዊ መረጋጋት እና መስማማት ነው’

ሰላም ጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን አዕምሮአዊ መረጋጋት እና መስማማት ነው -የደባርቅ ዮኒቨርስቲው መምህር ጌታቸው ውለታው

የሰላም ጉባዔ በባህርዳር በአማራ ክልል ምክርቤት እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው ስለ ሰላም ጥናት ያቀረቡት የደባርቅ ዮኒቨርስቲው መምህር ጌታቸው ውለታው እንዳሉት ሰላም ጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን አዕምሮአዊ መረጋጋት እና መስማማት ነው ብለዋል፡፡

ይሄ እውን የሚሆነው ደግሞ የህግ የበላይነትን እና እኩልነትን በማረጋገጥ ነው፡፡በዓለም ላይ የግጭት መነሻው ትልቁ ኢኮኖሚ ነው፡፡በወንዞች፣በመሬት እና ቅርሶች… ወዘተ በሚነሱ ፍላጎቶች ግጭቶች ይነሳሉ፡፡

ከሶማሊያ እስከ ሱዳን ከየመን እስከ ሶሪያ ባለው ግጭት ውስጥ የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ እና ማህበራዊ መሰረቶች መነሻ ሆነዋል፡፡
ግጭቶች በዲሞክራሲያዊ መንገድ ስላልተፈቱ ሃገር ወደ ማፍረስ ደርሰዋል ፡፡

እንደ መምህር ጌታቸው በኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭትም መነሻው የፍትሃዊነት ጉድለት ነው፡፡ ግጭት ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሃገርን ከማፍረስ እንዳይደርስ የዳኝነት ስራዓትን ፍትሃዊ ማድረግ እና ነፃ ሚዲያ መፍጠር በአማራጭነት ቀርቧል፡፡

በጉባዔው የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት የዲሞክራሲ ስራዓቱን ማስረፅ፣አማራጭ የግጭት መፍቻ መንገዶችን መጠቀም፣የውይይት እና የክርክር መድረኮችን በመጠቀም የግጭት መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን መቀነስ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ብናልፍ አንዷለም ሰላም የማህበረሰቡ አንድ ተፈጥሮአዊ እሴት በመሆኑ ሰላምን የሚያጓድሉ ጉዳዮችን ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የአማራ  ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ማሞ ምክርቤታችን ሰላምን የስራው ሁሉ መነሻ አድርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡


በየሺሀሳብ አበራ – አብመድ
ምስል፡- በአብርሃም በዕውቀት

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram