ሜሪካ ለሳዑዲ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው የጦር መሳሪያ መሸጥ የሚያስችለውን ስምምነት አጸደቀች
አሜሪካ ለሳዑዲ ዓረቢያ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የጦር መሳሪያ መሸጥ የሚያስችለውን ስምምነት አጸደቀች።
ስምምነቱ 670 ሚሊየን ዶላር ፀረ ታንክ ሚሳኤል፣ 106 ሚሊየን ዶላር የጦር ሄሊኮፕተር ጥገና እና የ300 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ ተሽከርካሪ ሽያጭን ያካተተ ነው ተብሏል።
የአሁኑ ሽያጭ ስምምነት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው አመት በሳዑዲ ዓረቢያ ባደረጉት ጉብኝት፥ ለሳዑዲ ዓረቢያ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለመፈጸም የያዙት እቅድ አካል ነው።
ስምምነቱ የአሜሪካን ወዳጅ ሃገራት የደህንነት አቅም በማጠናከር የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ደህንነት የሚያጠናክር መሆኑን፥ የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት አስታውቋል።
በርካታ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን የሽያጭ ስምምነቱን ተቃውመውታል።
ድርጅቶቹ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባውያን ሃገራት ለሳዑዲ ዓረቢያና ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚያደርጉትን የጦር መሳሪያ ሽያጭ በፅኑ አውግዘዋል።
ሃገራቱ የሚያደርጉት የጦር መሳሪያ ሽያጭ በየመን እየደረሰ ላለው ሰብዓዊ ቀውስ ጥቅም ላይ ውሏል በሚልም ይኮንናሉ።
ምንጭ፦ ፕረስ ቲቪ
Share your thoughts on this post