fbpx
AMHARIC

ሉሲዎቹ የሊብያ አቻቸውን በድምር ውጤት 15ለ0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎች) ለአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ የሊቢያ አቻቸውን ሚያዝያ 2 በአዲስ አበባ ስታዲየም አስተናግደዋል።

የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታም ዛሬ ሚያዝያ 2 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው የተካሄደው።

ጨዋታዉን በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎች) 7ለ0 አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው።

በጨዋታው ላይም ሎዛ አበራ በ27ኛ፣ 51ኛ፣ በ82ኛ እና በ87ኛ ደቂቃ ላይ አራት ጎሎችን ስታስቆጥር፤ ቀሪዎቹን ጎሎች ህይወት ደንጊሶ በ13ኛ ደቂቃ፣ ረሒማ ዘርጋ በ45ኛ ደቂቃ እንዲሁም ሰናይት ቦጋለ በ73ኛ ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

በ2018 ጋና ለምታስተናግደው የቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ የመጀመርያው ዙር የማጣርያ ጨዋታውን ካይሮ ላይ ከሊብያ አቻቸው ጋር የተጫወቱት ሉሲዎቹ 8ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት መመለሳቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም ሉሲዎቹ በድምር ውጤት 15ለ0 በማሸነው በቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ አሃዱ ካለበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ በመድረኩ መሳተፍ ሲችል፤ በአንጻሩ ሊቢያዎች አንድም ጊዜ ተሳትፈው አያውቁም።

የሊቢያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ላይ መሳተፍ የጀመሩት ባለፈው የ2009 ዓ.ም ካሜሮን ባዘጋጀችው ውድድር ሲሆን፤ በውድድሩም ማጣሪያውን ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram