ህንድ ቆራጥ እርምጃ ወሰደች
ከ 12 አመት በታች የሆናቸው ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ ሰዎች በህንድ ከዚህ በኋላ ሞት ይሆናል ቅጣታቸው፡፡ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ግን ይህ ቅጣት በቂ አይደለም ብለዋል፡፡ በመሆኑም ካቢኔያቸውን በአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ህጉ ከ 16 አመት በታች ሴቶችን የሚደፍሩትን ጭምር በሞት የሚቀጣ ተደርጎ እንዲጸድቅ የህግ ማሻሻያ አቅርበዋል ተብሏል፡፡
በህንድ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እጅግ አሰቃቂ ደረጃ ላይ የሚገኝና ከባድ የፖለቲካ ችግር እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው ይባላል፡፡ በቅርቡ የ 8 አመት ህጻን አሺፋ በቡድን ተደፍራ ከተገደለች ወዲህ ደግሞ ጉዳዩ መላውን ህንድ ሲንጥ ነው የቆየው፡፡ የናሬንድራ ሞዲ መንግስት ለዜጎች ግፊት መልስ ለመስጠት በሚል ነው ጠንካራ የሞት ቅጣትን በወንጀለኞቹ ላይ የደነገገው፡፡
Share your thoughts on this post