fbpx

ፕሮቲን በብዛት አዘውትሮ መውሰድ ለአጥንት ጤና ጠቃሚ ነው- ተመራማሪዎች

በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትሮ መውሰድ የአጥንት መጠንን እንዳይቀንስ እና በቀላሉ እንዳይሰበር ያደርጋል ሲል አንድ ጥናት አመለከተ።

አዲሱ ጥናት እንዳመለከተው በፕሮቲን የበለፀገ ምግብ አዘውትረው የሚጠቀሙ ጎልማሳ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ በቂ ካልሽየም ስለሚኖር ጤናማ አጥንት ይኖራቸዋል።

እንዲሁም ፕሮቲን አዘውትረው የሚጠቀሙ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ አጥንታቸውን ሊጎዳ የሚችል አሲድ ስለማይኖር ጥናቱ አመልክቷል።

በዚህ ጥናት ፕሮቲን አዘውትረው የሚወስዱ ሰዎች የአጥንት ስብራት እንደቀነሰላቸው እና በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘው የካልሽየም መጠን እንደጨመረ አመልክቷል።

ከዚህ ባለፈ ፕሮቲኑ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን እና አጥንትን ጠንካራ እንዲሆን የሚያስችለው የአጥንት ማዕድን መጠን ተመጣጣኝ አድርጎታል።

በበቂ ሁኔታ ፐሮቲን እና ካልሽየምን መውሰድ የህፃናትን አጥንት እድገት የተሻለ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን፥ በሁሉም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች አጥንት ጤናማነት ወሳኝ ነው ተብሏል።

ተመራማሪዎች በብዛት በፕሮቲን የበለፀገ ምግብን መውሰድ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን የአሲድ መጠን ከፍተኛ ያደርገዋል የሚለውን እይታ ጥናቱ ውድቅ አድርጓል ብለዋል።

በዚህም ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሰው በብዛት በፕሮቲን የበለፀገ ምግብ መውሰድ ሳይሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ፕሮቲን ዝቅተኛ መሆን እንደሆነ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

ጥናቱ በፕሮቲን የበለፀገ የአትክልትም ሆነ የእንስሳት ምግብ ከካልሽየም ጋር ተመጣጣኝ አድርጎ መውሰድ ለአጥንት ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክቷል።

ምንጭ፦ ሳይንስዴይሊ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram