ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ጋር የመገናኘት እቅዳቸውን ሰረዙ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የመገናኘት እቅዳቸውን ሰረዙ።

ፕሬዚዳንቱ በፈረንጆቹ ሰኔ 12 ሲንጋፖር ላይ ሊካሄድ የታቀደው ውይይት እንደማይካሄድ አረጋግጠዋል።

ይህንንም የወሰኑት ሰሞኑን ከሰሜን ኮሪያ ወገን ሲሰነዘሩ የነበሩት የጥላቻ ንግግሮችን መሰረት አድርገው መሆኑን ለኪም ጆንግ ኡን በላኩት ደብዳቤ ላይ አስፍረዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ወደፊት ተገናኝቶ የመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ነገር ግን በደብዳቤያቸው ላይ ፕሬዚዳንቱ “እርሶ ስለታጠቁት የኑክሌር ጦር መሳሪያ አቅም ይናገራሉ፤ ነገር ግን እኛ ያለን ሰፊ እና ሀያል ነው” የሚልንም አስፍረዋል።

ዛሬ አንድ የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት የሰሜን ኮሪያ ፍፃሜ እንደ ሊቢያ ይሆናል በሚል ለሰጡት አስተያየት ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram