fbpx
AMHARIC

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አዲስ የደህንነት አማካሪ ሾሙ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የደህንነት አማካሪ መሾማቸውን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ የቀድሞውን የደህንነት አማካሪ ሬይሞንድ ማክማስተርን በጆን ቦልተን መተካታቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ የቦልተን ሹመት በትዊተር ገጻቸው ያስታወቁ ሲሆን ማክማስተርንም አመስግነዋል።

ቦልተንም ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አዲሱ ተሿሚ ጆን ቦልተን ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳዳር ሆነው አገልግለዋል።

በተጨማሪም ቦልተን በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቀማሪነታችው የሚታወቁ ሲሆን፥ የሮናልድ ሬገን አስተዳደርን ጨምሮ በሁለቱ ቡሾች የስልጣን ዘመን ለሃገራቸው ሰርተዋል።

ጆን ቦልተን በኢራንና በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ከትራምፕ ጋር ተመሳሳይ አቋም የሚያንጸባርቁ ሲሆን፥ በሃገራቱ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ቢወሰድ ፍላጎታቸው መሆኑም ይነገራል።

የ69 ዓመቱ ቦልተን ትራምፕ በ 14 ወራት ውስጥ የሾሟቸው ሶስተኛው የደህንነት አማካሪ ሆነዋል።

አዲሱ ሹመት ያለሴኔቱ ድጋፍ ማለፍ የሚችል በመሆኑ በያዝነው ወር መገባደጃ ላይ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ሳምንት ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቲሊርሰንን አባረው የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር የነበሩትን ማይክ ፖምፔን መሾማቸው የሚታወስ ነው።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram