fbpx

ፕሬዚደንት ኢሳያስ ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተዋል

ኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዚደንት ኢሳያስ በንጉስ ሰልማን በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀኑት ተብሏል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ ጉዳዮችና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ከፕሬዚደንቱ ጋር የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህና አማካሪያቸው የማነ ገብረአብ መጓዛቸውን ከሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከ20 ቀናት በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በቆታቸውም ፕሬዚዳንቱና ሼህ ሙሀመድ ቢን ዛያድ አል ናህያን በሁለቱ ሀገራት የጋራ በሆኑ ነጥቦች ፣ በአካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በንግድ እና ኢንቨስትመንት በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም መወያየታቸው ተነግሯል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram