fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ፕሪሚየር ሊጉ በ2ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይመለሳል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይመለሳል።

ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታች መካከል ፋሲል ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያረጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሁለቱ ቡድኖች አዲግራት ላይ ያደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቁ የሚታወስ ነዉ።

ከአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ውጭ የሆነዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊጉ መሪ ደደቢት ያለዉን የስድስት ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ድሬዳዋ ጋር ይጫወታል

ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመከላከያ ሃዋሳ ከተማ ከጂማ አባ ጅፋር እንዲሁም ወልዲያ ከተማ ከአዳማ ከተማ ሌሎች ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎቸ ናቸው።

ፕሪሜርሊጉ ነገም ቀጥሎ ሲከናወን በዛማሌክ ላይ ድል ያስመዘገበዉ ወላይታ ድቻ ከሊጉ መሪ ደደቢት ጋር ይጫወታል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram