fbpx

ፑቲን ሩሲያንና ክሬሚያን የሚያገናኘውን አወዛጋቢ ድልድይ ከፈቱ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደቡባዊ ሩሲያንና ክሬሚያን የሚያገኛኘውን አወዛጋቢውን ድልድይ ከፈቱ፡፡

ድልድዩ 19 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፥ አውሮፓ ካለው ትልቁ የቫስኮዳጋማ ድልድይ እንደሚልቅ ተገልጿል፡፡

ይህ 3 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ዶላር የወጣበት ድልድይ፤ ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት ጊዜ በስደስት ወራት ቀደም ብሎ መጠናቀቁን ነው የገለጹት፡፡

ዩክሬን ግንባታውን የተቃወመች ሲሆን፥ አካባቢውን እንደሚጎዳና ግዙፍ መርከቦችን ወደ ወደቧ እንዳታስገባ እንደሚያግዳት አስታውቃለች፡፡

የአውሮፓ ህብረትና ዩናይትድ ስቴትሰስ በግንባታው ላይ የተሳተፉትንና ጨረታ ባሸነፉት ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ታወሳል፡፡

ድልድዩ ክሬሚያ ምግብና የተለያዩ ቁሳቁሰሶችን ከሩሲያ ለማግኘት ይረዳታል ተብሏል፡፡

ከአራት ዓመታት በፊት ክሬሚያ በሪፈረንደም ከሩሲያ ጋር የተቀላቀለች ሲሆን፥ ምዕራባውያንና ዩክሬን ተቀባይነት የሌለው ወረራ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ዩኤስኤቱዴይ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram