የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን እና የቼልሲ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ፍራንክ ላምፓርድ የደርቢ ካውንቲ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።
ላምፓርድ የእንግሊዝ ሁለተኛው ሊግ ውስጥ የሚጫወተው ደርቢ ካውንቲ ክለብ አሰልጣን የሆነው የክለቡ አሰልጣኝ ጋሪይ ሮዌት ክለቡን ለቀው ወደ ስቶክ ሲቲ በማቅናታቸው ነው።
የ39 ዓመቱ ፍራንክ ላምፓርድ በትናንትናው እለትም በክለቡ የሚያቆየውን የ3 ዓመት ኮንትራት ውል መፈራረሙ ተነግሯል።
ላምፓርድ የአሰልጣኝነት ስራውን ያገኘው ክለቡን ለማሰልጠን ካመለከቱ 20 ሰዎች መካከል ነው የተባለ ሲሆን፥ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥም የደርቢ ካውንቱ ክለብ 7ኛ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።
የአሰልጣኝነት ስራውን በደርቢ ካውንቲ ክለብ ሀ ብሎ የሚጀምረው ላምፓርድ እድሉን በማግኘቱ ደስተኛ መሆኑን አስታውቋል።
በሌላ ዜና ኤቨርተን ማርኮ ሲልቫን አዲሱ አሰልጣኙ አድርጎ መሾሙም ተነግሯል።
የ40 ዓመቱ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ወደ ጉዲሰን ፓርክ የመጡት የኤቨርተን ክለብ ባለቤት ፋርሃድ ሞሾሪ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስን በውድድርን ዘመኑ መጨረሻ ማሰናበታቸውን ተከትሎ ነው።
የኤቨርተን ክለብ ባለቤት ፋርሃድ ሞሾሪ አሰልጣኝ ሮናልድ ኩመንን ባለፈው ጥቅምት ወር ከክለቡ ማሰናበታቸውም አይዘነጋም።
አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ልምድ ያላቸው ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም ሁል ሲቲን እና ዋትፎርድን አሰልጥነው ነበር።
ምንጭ፦ ቢቢሲ