ፌስ ቡክ ደንበኞቹ የሰዓት አጠቃቀማቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ አገለግሎት ላይ ሊያውል ነው

ፌስ ቡክ ደንበኞቹ የሰዓት አጠቃቀማቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ሊያውል መሆኑን ገልጿል።

መተግበሪያው የፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በእየቀኑ ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎቹ በእየቀኑ ለመጠቀም የሚፈልጉትን ጊዜ ለመወሰን፣ ለማስታወስና አማራጭን ለማስተካከል ያስችላል ተብሏል።

በባለፈው ዓመትም ኩባንያው ደንበኞቹ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ለህዎታቸው ገንቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደረጉ ሰዓታቸውን ለመቆጠጠር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ እየሰራ መሆኑን መግለጫ ሰጥቶ የነበረ መሆኑን ዘገባው አስተውሷል።

የፌስቡክ ኩባንያ አዲሱ መተግበሪያ ደንበኞቹ ሰዓታቸውን በፕሬግራምና በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል እንደሆነም ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

 

ምንጭ፦ telegraph.co.uk

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram