fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ፌስ ቡክ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንደማይፈጽም ገለጸ

ፌስ ቡክ ካምብሪጅ አናሊይቲካ በደንበኞቹ ላይ አደረሰ ከተባለው የመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የካሳ ክፍያ እንደማይከፍል አስታውቋል።

ኩባንያው ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ የማይፈጽም መሆኑን የገለጸው ከዚህ ሳምንት በፊት በብራሰልስ የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች ለኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግ የክፍያ ከሳን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በተሰጠ የጽሁ ምላሽ ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች የህብረቱ ሀገራት የፌስ ቡክ ደንበኞች ከመረጃ ብርበራው ጋር በተያያዘ የካሳ ክፍያ መከፈል አለባቸው የሚል ጥያቄ ለኩባንያው ማቅረባቸውን ዘገባው አመላክቷል።

ኩባንያው በበኩሉ የመረጃ ብርበራው የደንበኞችን መብት የሚጥስ ቢሆንም በደንበኞቹ የባንክ ሂሳብና ሌሎች ከገንዘብ ጋር የተያያዙ መረጃዎች ያለመበርበራቸውን ገልጿል።

የህብረቱ አባል ሀገራት ደንበኞች መረጃ ስለመበርበሩም መረጃ ያለመኖሩንም አስታውቋል ነው የተባለው።

ካምብሪጅ አናሊይቲካ በሚሊየን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ደንበኞቹን መረጃ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ማዋሉን ዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ፦ phys.org/news

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram