fbpx

ፌስቡክ ከ500 ሚሊየን በላይ የሀሰት ገፆችን መዝጋቱን አስታወቀ

ፌስቡክ በአውሮፓውያኑ 2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከግማሽ ቢሊየን በላይ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆችን መዝጋቱን አስታውቋል።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን መብት የሚጋፉ እና የጥላቻ ንግግሮች በሚያሰራጩት ላይ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩን ተከትሎ ነው እነዚህ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች ተለይተው የተዘጉት ተብሏል።

እንደ ፌስቡክ ገለፃ ከሆነ እርምጃ የሚወሰድባቸው የፌስቡክ ገፆች ቁጥር አሁንም ከዚህ ሊጨምር ይችላል።

ፌስቡክ አክሎም አመፅ ቀስቃሽ ይዘት ያላቸው 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ፌስቡክ ላይ የተለቀቁ ይዘቶች ላይም ማስጠንቀቂያ አሊያም ከገጹ ላይ የማውረድ እርምጃ እንደተሰወዳቸው አስታውቋል።

ከእነዚህ ውስጥ 85 በመቶው ይዘቶች በርካታ ሰዎች ጋር ሳይደርሱ ከፌስቡክ ላይ እንዲሰረዙ መደረጉን ነው ኩባንያው የገለፀው።

የጥላቻ ንግግርን በተመለከተም በፈረንጆቹ 2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የጥላቻ ንግግሮችን ከገፁ ላይ ማንሳቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

ከአሸባሪዎች ጋር በተያያዘም በሩብ ዓመቱ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን የሽብር ይዘት ያላቸው ፖስቶች ከፌስቡክ ላይ እንዲነሱ መደረጉም ተነግሯል።

ግልጽ የሆኑ ወሲባዊ እንቅስቃሴዎችን የያዙ 21 ሚሊየን ይዘቶችም ባለፉት ሶስት ወራት በተደረገ ቁጥጥር ከፌስቡክ ላይ እንዲነሱ ማድረጉንም ፌስቡክ ገልጿል።

የፌስቡክ የምርት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ገይ ሮዘን፥ አሁንም ቢሆን በፌስቡክ ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች ይቀራሉ ብለዋል።

ይህ ስራም በቀጣይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት ቴክኖሎጂ እና በሰዎች ታግዞ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ነው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ያስታወቁት።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram