fbpx
AMHARIC

ፋና ቴሌቪዥን ዲ ኤስ ቲቪን ተቀላቀለ

(ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ቴሌቪዥን በአለም አቀፉ የመዝናኛና የመረጃ ቻናል ዲ ኤስ ቲቪ መታየት ጀመረ።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን እያተረፈ የሚገኘው ፋና ቴሌቪዥን ከዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም፥ ጀምሮ በይፋ ዲ ኤስ ቲቪን እንዲቀላቀል መደረጉን መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ ለጣቢያችን በላከው ደብዳቤ ገልጿል።

ይህም ፋና ቴሌቪዥን የስርጭት አድማሱንና ተደራሽነቱን እንዲያሰፋ የሚያስችለው ይሆናል።

ለፋና ቴሌቪዥን ተከታታዮችም ሃገራዊና አለም አቀፋዊ ቻናሎችን በአንድ ላይ የማግኘት እድልንም ይፈጥርላቸዋል።

መልቲ ቾይዝ በ49 የአፍሪካ ሃገራት የተለያዩ ስፖርታዊ፣ የመዝናኛና የመረጃ ቻናሎችን በዲ ኤስ ቲቪ አማካኝነት ያቀርባል።

ዲ ኤስ ቲ ቪ በአሁኑ ሰአት ያሉትን ከ100 በላይ አለም አቀፋዊ ቻናሎች በተለያዩ አምስት አማራጭ ጥቅሎች አማካኝነት እያቀረበም ይገኛል።

የፋና ቴሌቪዥን ዲ ኤስ ቲ ቪን መቀላቀልም ተጨማሪ እና አማራጭ የስርጭት መድረክ ለተመልካቾቹ ይፈጥራል።

የተለያዩ አለም አቀፍ የቴሌቪዥን ቻናሎች ከዚህ ቀደም ዲ ኤስ ቲቪን መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram