ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታ ጥያቄ አቀረበ

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ከሚጫወት ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ አቅርቧል።

ክለቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን የባህል፣ የኢኮኖሚ እና የጋብቻ ትስስር እና ቁርኝት በስፖርትም ቀደም ሲል የነበረውን ወንድማማችነትና ፍቅር ለማስቀጠል በሚል ነው የወዳጅነት ጥያቄውን ያቀረበው።

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በላከው ደብዳቤም አኤርትራ ከሚገኝና በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ከሚጫወት የእግር ኳስ ክለብ ጋር አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

ክለቡ በደብዳቤው፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርና በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተጀመረውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የማጠናከር ስራን ለመደገፍ ጥያቄውን ማቅረቡን አስታውቋል።

fasil.jpg

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram