ጨፌ ኦሮሚያ ሊያካሂድ የነበረውን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ለሌላ ጊዜ አዛወረ
ጨፌ ኦሮሚያ ሊያካሂድ የነበረውን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ወደ ሌላ ጊዜ ማዛወሩን የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚካሄድ መነገሩ ይታወሳል።
የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን እና የመረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአካባቢው ያለው የሰላም ሁኔታ የተረጋጋ ባለመሆኑ የጨፌው መደበኛ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የሚካሄድበትን ቀን አስመልክቶ ወደ ፊት ለጨፌው አባላት በሚደረግ ጥሪ የሚታወቅ መሆኑንም አቶ ሀብታሙ አስታውቀዋል።
Share your thoughts on this post