በነብስ አድን መርከብ ተጭነው በሜዲትሪያን ባህር ላይ ከጣልያንና ማላላ የተገፉ ከ6መቶ በላይ ስደተኞች በስፔን ቫሌንሲያ ወደብ ላይ ደርሰዋል።
የስፔን መንግስት ለስደተኞቹ ነጻ የጤና አገልግሎት እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ለያንዳንዱ የጥገኝነት ጉዳይ ግን ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ጣልያንና ማላላ አንቀበልም ያሏቸው ስደተኞችን እንደሚቀበሉ የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ስደተኞችን በጫነችው አኳሪየስ በተባለች መርከብ ውስጥ ህፃናት እና ነፍሰ ጡሮች እንደነበሩበት ተመልክቷል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
Share your thoughts on this post