fbpx

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሃዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ እና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግጭት በተፈጠረባቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አካባቢዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገው እለት በሃዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩ ይሆናል።

ከነገ በስቲያ ረቡዕ ደግሞ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት ከከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ።

ውይይቱ በከተሞቹ ባለፉት ቀናት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሚደረግ ነው።

ባለፉት ቀናት በሃዋሳ፣ ወልቂጤ እና ወላይታ ሶዶ በተፈጠሩ ግጭቶች 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ መንግስት መግለጹ የሚታወስ ነው።

በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ በርካታ የንግድ ተቋማት ላይ ዝርፊያ መፈጸሙም ነው የተነገረው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት በሰጡት ማብራሪያ፥ በእነዚህ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የተቀነባበሩ መሆናቸውን መናገራቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንዱን ብሄር ከሌላው በማጋጨት ሃገር መገንባት እንደማይቻል ጠቅሰው፥ የዜጎችን ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት መብት ከማስጠበቅ አንጻር የተሰሩ ስራዎች ውስን መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም መንግስት ይህን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ አስረድተዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram