fbpx

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጸጉረ-ልውጥ ያሏቸውን ሰዎች ወጣቶች በንቃት እንዲከታተሉ ጥሪ አቀረቡ


ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ጸጉረ-ልውጥ ያሏቸውን ሰዎች ወጣቶች በንቃት እንዲከታተሉ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ምኒስትሩ “በአዳጊ ክልሎች አዳዲስ ኃይሎች አዳዲስ ሰዎች ጸጉረ-ልውጥ ሰዎች እየተንቀሳቀሱ የሚያደራጁት ኃይል ካለ ስርዓቱ ብቻ ሳይሆን ወጣቶች ቆቅ ሆነው እንዲጠብቁ” ሲሉ በዛሬው ዕለት ለብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ በታዳጊ ክልሎች የእርስ በእርስ ግጭት ለመቀስቀስ እየተሰሩ ያሉ ሴራዎችን ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

በመንግስት በኩል የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ በየአካባቢው እየተደረጉ ላሉ ሰላማዊ ሰልፎችም ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይ ህብረተሰቡ ሰልፉን ገታ በማድረግ ሙሉ ኃይሉን ወደ ልማት ሥራዎች እንዲመልስ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰላሙን ለመመለስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተጨባጭ ስራ ለሰሩት ወገኖች ምስጋና አቅርበዋል።

“አዳዲስ ሰዎች አካባቢያቸው ገብተው ከወጡ በኋላ የሚያጋጥሙ ችግሮች እየተበራከቱ ስለሆነ በመንግሥት የምናደርገው እንደተጠበቀ ሆኖ ሕዝቡ ግን ጸጉረ-ልውጥ ሰዎች ሲመጡ የት፣ለምን፣ ከማን ጋር እንደሚገናኙ እና ምን እንደሚያደርጉ መከታተል እና የአካባቢያቸውን ሰላም መጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አደራ ማለት እፈልጋለሁ” ሲሉም አክለዋል።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ አመራር ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ያመጡትን ለውጥ በመደገፍ ሚሊዮኖች አደባባይ በመውጣት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram