fbpx

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከጋምቤላና ደምቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳምንቱ መጨረሻ ከጋምቤላና ደምቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ሲያቀኑ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናትም አብረው እንደሚጓዙ ተነግሯል።

በደምቢ ዶሎ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ግንባታቸው የተጠናቀቁትን የደምቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ እና የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲን በይፋ እንደሚመርቁም ይጠበቃል።

እንዲሁም ከደምቢ ዶሎ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ጋምቤላ ክልል ያቀናሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋምቤላ ቆይታቸው ከክልል ከተወጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በጋምቤላ ከተማ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚያደርጉም ይሆናል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram