የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወርቅ ሜዳሊያ ከተመረቁ ተማሪዎች ጋር ሊገናኙ ነው።
ለዘንድሮ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪዎች የሚሳተፉበት መሰናዶ መዘጋጀቱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ዝግጅቱም ከፊታችን ሐምሌ 16 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ መሆኑንም ገልጿል።
በዝግጅቱ ላይም ከሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የተውጣጡ 400 የሚጠጉ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች መጋበዛቸንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተገኝተው ከተመራቂ ተማሪዎቹ ጋር የውይይት ጊዜ እንደሞኖራቸውም ተገልጿል።
በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ታዋቂ ግለሰቦች በዝግጅቱ ላይ እንደሚታደሙም ጽፍሀት ቤቱ አስታውቋል።
ተመራቂዎቹ ከውይይቱ በኋላም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን እና የቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ ተለያዩ ተቋማትንና መስሪያ ቤቶችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።
Share your thoughts on this post