fbpx

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋ ወራሽ ጋር በአቡ ዳቢ መከሩ

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሀገሪቱን አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን አል ነኸን ጋር በአቡ ዳቢ ተወያይተዋል።

በዚህም ወቅት ሁለቱ ሀገራት ወዳኝነታቸውን እና ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ እንዲሁም በወቅታዊ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጠንካራ እና ልዩ ነው ስላሉት ስለኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት በማንሳት፥ ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየተጠናከረ እንደሚሄድ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሀገራቱ በጋራ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉባቸውን የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር እድሎችን አንስተዋል።

አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን አል ነኸን በበኩላቸው ሀገራቸው ከወዳጅ ሀገራት ጋር እኩል ተጠቃሚነትን፣ መከባበርን እና መተባበርን መሰረት ያደረገ ጠንካራ ፖሊሲ እንዳላት አንስተዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነታቸውን ወደፊት ለማስኬድ ባላቸው ፍላጎት ምክንያት ይህን መልካም ወዳጅነታቸውን እያሻሻሉት መምጣታቸውን አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram