fbpx

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በሳዑዲና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፍሪካ ውጪ የመጀመሪያቸው የሆነውን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሀሙስ ጀምሮ ባካሄዱት ጉብኝት ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ጎብኝተዋል።

በሳዑዲ ቆይታቸው ከሀገሪቱ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይቱ ሁለቱ ሀገሮች ትርጉም ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለመፍጠር እንዲሁም በሀይል ልማት እና ግብርና ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች በቁጥጥር ስር ውለው በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እንዲፈታ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።

በመቀጠልም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሀገሪቱ አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን አል ነኸን ጋር በአቡ ዳቢ ተወያይተዋል።

በዚህም ወቅት ሁለቱ ሀገራት ወዳኝነታቸውን እና ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ እንዲሁም በወቅታዊ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጠንካራ እና ልዩ ነው ስላሉት ስለኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት በማንሳት፥ ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየተጠናከረ እንደሚሄድ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram