የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለተለያዩ የፌደራል መንግስት የስራ ሀላፊዎች ሹመት ሰጡ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መሰረት፦
1. አምባሳደር ደግፌ ቡላ- በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትህና የህግ ምርምር እና ስልጠና ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር
2. አቶ ፍቃዱ ተሰማ- በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባባሪያ ማዕከል አስተባባሪ
3. አቶ ሳዳት ናሻ- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል
4. አቶ ዛዲግ አብርሃ- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል
5. ዶክተር ተመስገን ቡርቃ- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል
6. ወ/ሮ ለሃርሳ አብዱላሂ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ
7. አቶ ብርሃኑ ፈይሳ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ
8. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ – የግብርናና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ
9. ዶ/ር ኢያሱ አብርሃ – የግብርናና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ
10. አቶ ሲሳይ ቶላ – የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዴኤታ
11. ዶ/ር መብራቱ ገብረማሪያም – የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዴኤታ
12. አቶ እሸቴ አስፋው – የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
13. ወ/ሮ ህይወት ሞሲሳ – የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
14. ዶ/ር ነጋሽ ዋቅሻው – የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዴኤታ
15. ዶ/ር አብርሃ አዱኛ – የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዴኤታ
16. አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ
17. አቶ አያና ዘውዴ – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ
18. አቶ ቴድሮስ ገብረእግዚአብሄር – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
19. አቶ ከፍያለው ተፈራ – የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ
20. አቶ ካሳሁን ጎፌ – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዴኤታ
21. አቶ ተመስገን ጥላሁን – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዴኤታ
22. ዶክተር መብራህቱ መለስ – የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ
23. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ – የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ
24. አምባሳደር ሌላዓለም ገብረዮሐንስ – የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ
25. አቶ ጌታቸው ኃይለማሪያም- የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ
26. አቶ አድማሱ አንጎ- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሚኒስትር ዴኤታ
27. አቶ ገለታ ስዮም- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሚኒስትር ዴኤታ
28. አቶ አህመድ ቱሳ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ
29. አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
30. አቶ አሰፋ ኩምሳ – የማእድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋር ሚኒስትር ዴኤታ
31. ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ
32. ወ/ሮ ቡዜና አልከድር- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ
33. ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
34. አምባሳደር ብርቱካን አያኖ -የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
35. ወ/ሮ አስቴር ዳዊት – የሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
36. ወ/ሮ ፍሬህይወት አያሌው – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
37. ወ/ሮ ፈርሂያ መሐመድ – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
38. ወ/ሮ ምስራቅ ማሞ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
39. ወ/ሮ ስመኝ ውቤ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
40. አቶ ጌታቸው ባልቻ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
41. ኮሎኔል ታዜር ገ/እግዚዓብሔር – የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ
42. ወ/ሮ ኢፍራን ዓሊ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ
43. አቶ ወርቁ ጓንጉል – በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የጽ/ቤት አገልግሎትና መልካም አስተዳደር ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ከግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙ ሲሆን የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ ነው።