fbpx

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ 2 ሺህ ከሚበልጡ የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይም 2 ሺህ 400 የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች መካፈላቸው ተገልጿል።

PM_omn.jpg

በውይይት መድረኩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እና ገለፃ ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በመቻቻል፣ በመከባበር እና በሌሎች የኢትዮጵያ እሴቶች ዙሪያም ለመድረኩ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram