fbpx

ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።

መተግበሪያው የሞባይል ኔት ወርክ የማስፋፋት ውስንነት ባለባቸውና የበይነ መረብ መቆራረጥ ችግር የሚያጋጥማቸው አካባቢዎችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በተለያዩ አካባቢዎች ተፈላጊነት ያላቸውን አርቲክሎች እየመረጠ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይኖርበት ጊዜ ለማንበብ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው።

ከዚህም ሌላ ደንበኞቹ ወደ ጎግል አካውንታቸው ሲገቡ ከሚጠቀሟቸው ልምዶች በመነሳት የበይነ መረብ አገልግሎቱ በሌለበት ጊዜ ለማንበብ የሚፈልጓቸውን መረጃዎች እንደሚሰበሰብ ነው የተገለጸው።

መተግበሪያው ህንድ ብራዚል ኢንዶኖዥያን ጨምሮ ለ100 ያህል ዓለም ሀገራት አገልግሎት እንደሚሰጥም ነው የተገለጸው።

መተግበሪያው በዚህ መልኩ አሁን ላይም አርቲክሎችን ለማንበብ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነ ዘገባው አመላክቷል።

የጎግል አዲሱ መተግበሪያ በክሮም ብሮውዘር አንድሮይድ ኦፕሬቴንግ ሲስተም አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ የዋይ ፋይ አገልግሎት እንዳገኘ መተግበሪው በራሱ ጠቃሚ  መረጃዎችን ‘‘ዳውን ሎድ’’ በማድረግ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይኖርበት ጊዜ ለመጠቀም እንደሚያስችል ነው የተገለጸው።

 

ምንጭ፦ techworm.net

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram