ግብፅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለ3 ወራት አራዘመች

ግብፅ በሀገሪቱ ተግባራዊ እየሆነ ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ሶስት ወራት አራዘመች ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ ሶስት ወራት መራዘሙም በሀገሪቱ በፕሬዚዳንት አንዱል ፈታህ ኤልሲሲ በኩል ማሳወቋ ተነግሯል ።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም ያስፈለገውም ለሀገሪቱ ፀጥታ ችግር የሆኑ አካላትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ያለመ ነው ተብሏል።

የአሸባሪው እስላሚክ ስቴት አካል ነኝ በሚል ቡድን በኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የሽብር ጥቃት ተፈጽሞ በርካቶች ከሞቱ ወዲህ እስካሁን በአስቸኳይ ጊዜ ውስጥ እንዳለች ይታወሳል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ሚያዚያ ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጅም በተለያዩ ጊዜያት ሲራዘም ቆይቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፀጥታ አካላት ከሽብር ጋር በተያያዘ የጠረጠሯቸውን ሰዎች ያለምንም ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ የሚያስችላቸው ነው።

ከዚህ ባለፈም የአል ሲሲ አስተዳደር በመገናኛ አውታሮች ላይ ያለምንም ገደብ ቁጥጥር እንዲያደርግ ያስችለዋል።

ግብጽ ባለፉት አመታት በተለይም በሲና በረሃ ከመሸጉ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እያስተናገደች ትገኛለች።

ምንጭ፦ apnews.com

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram