fbpx

“ጊዜ ያስፈልገኛል! ገና እኮ ሁለት ወሬ ነው። ውዝፍ እና ክምር ጭናችሁብኝ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው?” ዶ/ር አብይ አህመድ

“ጊዜ ያስፈልገኛል! ገና እኮ ሁለት ወሬ ነው። ውዝፍ እና ክምር ጭናችሁብኝ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው?” ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ በመገኘት ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሀዋሳ ከተማ የተፈጠረው ግጭት የሲዳማን ህዝብ አይወክልም ያሉ ሲሆን፥ የችግሩ ፈጣሪዎች ተለይተው ለህግ እንዲቀርቡ እና እርቅ መፈፀም እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ተሳታፊዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቧቸውቄዎች የሲዳማ ብሄር ራስን በራስ የማስተዳደር ወይም የክልል ጥያቄ አንዱ ሲሆን፥ ይህ ጉዳይ ለ12 ዓመታት ሲንከባለል መቆየቱን እና እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን አንስተዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ ያለመሆን፣ በልማት ምክንያት የሚነሱ አርሶ አደሮች ተገቢውን የካሳ ክፍያ እያገኙ አይደሉም የሚለው እና የወጣቶች የስራ አጥነት ችግር በጥያቄነት የቀረቡ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ፥ የፊቼ ጨምበላላን በዓልን ተከትሎ በሀዋሰ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ሊፈጠር የማይገባው እና መሆን ያልነበረበት ነው ብለዋል።

ግጭቱ እንዲቆም ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎም ግጭቱ እንዳይባባስ አስተዋፅኦ ላደረጉ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች እና ሌሎች አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉ አካላት የሲዳማ ህዝብ ጠላት ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ግጭት እንዲፈጠር እና ለሰው ደም መፍሰስ ምክንያት የሆኑ ግለሰቦችን መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለህግ ያቀርባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ነው ያሉ ሲሆን፥ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ለማንሳት ህገ መንግስቱ ይፈቅድለታል ብለዋል።

ነገር ግን ጥያቄው በህገ መንግስታዊ መንገድ መቅረብ እንደሚገባው እና መፍትሄ የሚያገኘውም ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ እንደሆነም አንስተዋል።

“እናንተም ለምን ክልል መሆን አስፈለገን ብላችሁ ከታች እስከ ላይ በሚገባ ተወያዩ እኛም እንወያያለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሰጡት ማብራሪያ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ለሲዳማ ህዝብ የሚታገሉ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችም ወደ ሀገር ቤት ገብተው ሰላማዊ ትግል አንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

እሰረኞች ይፈቱ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፥ እስረኞችን በመፍታት በኩል በፌደራል ደረጃ የተጀመሩ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አሉ፤ ክልሉም በዚህ ላይ ሊሰራ እንደሚገባው አስታውቀዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግረን በተመለከተም ችግሩን የሚፈጥሩት የፖለቲካ ነጋዴዎች ናቸው ናቸው፤ ከዚህ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ይገባልም ብለዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram