fbpx

“ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ሊደረግ ነው፡፡” የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት

ባለፉት ሶስት አመታት በአማራ ክልል በተፈጠሩ ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አጋርነቱን በማሳየት ዘመዶቻቸው ለሞቱባቸው ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ብር ከባድ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ 50 ሺህ ብር ፤ቀላል የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው 25 ሺህ ብር እንደሚሠጥ አስታውቋል፡፡

ብድር ተበድረው በልማት ስራ የተሰማሩ በተፈጠረው ግጭት ስራቸውን ማከናወን ያልቻሉ ከአብቁተ የተበደሩት ብድር ካለ የመክፈያው ጊዜ እንዲራዘምላቸው የክልሉ መንግስት መወሰኑን ዳይሬክተሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

የአማራ ክልል መንግስት መሰል ችግሮች እንዳይደርሱ ከአጎራባች ክልሎች ጋር እና ከህብረተሰቡ ጋር ምክክር የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram