ጃኮብ ዙማ ከሙስና ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከሙስና ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ መሆኑን የሃገሪቱ አቃቢ ህግ ዳይሬክተር አስታወቀ፡፡
አቃቤ ህግ ዙማ 18 በሚደርሱ የሙስና ክሶች እንደሚጠየቁ ገልጿል፡፡
እንዲሁም 700 በሚደርሱ ማጭበርበሮችና ህጋዊ ባልሆነ የገንዘብ ዝውውር እንሚከሰሱም ጠቅሷል፡፡
ዙማ ከሚነሱባቸው ክሶች መካከል ፕሬዚደንት ከመሆናቸው በፊት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990ዎቹ የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ከፈረንሳይ ኩባንያ ጋር ስምምነት የፈጸሙበት ጉዳይም ዋነኛው ነው ተብሏል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘም የቀድሞ የዙማ የኢኮኖሚ አማካሪ ዘብጥያ ወርደው ነበር፡፡
ታዲይ የፍርድ ሂደቱ በዙማ የቅድመ ምርጫ ውድድር ወቅት እንደመከሰቱ አስደንጋጭ የነበረ ሲሆን÷ በቴክኒካል ምክንያት ክሱ ውድቅ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የ75 ዓመቱ ዙማ ባለፈው ወር በፓርቲያቸው ግፊት ከስልጣን መውረዳቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፦ሬውተርስና ቢቢሲ
Share your thoughts on this post