ጀሶን ከዱቄት እና አብሲት ጋር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው የሸጡት ባል እና ሚስት በእስራት ተቀጡ

ጆሶን ከዱቄት እና አብሲት ጋር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው ለግለሰቦች እና ድርጂቶች ሲሸጡ ነበር የተባሉት ባልና ሚስት በእስራት እንዲቀጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳለፈ።

በአራዳ ክፍለከተማ በቀበሌ 07 /08 በተለምዶ ዘበኛ ሰፈር እየተባለ በሚጠራ አካባቢ በቤት ቁጥር 801 የሚኖሩት ባልና ሚስቱ አቶ ሰናይ አበራ እና ወ/ሮ ሰሚራ አማን በሶስት ክስ ማለትም የጸና ንግድ ፍቃድ ሳይኖር እንጀራ መጋገር፣ መነገድ ፣ ለሰው ደህንነት አደጋ የሆነ ጀሶ የተቀላቀለበት እንጀራ ጋግሮ ለግለሰብና ለድርጅት በመሸጥ ፣ ከቆጣሪ ውጪ ከኤሌትሪክ መስመር ሃይል በጋራ ስርቆት ወንጀል በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል።

አቶ ሰናይ አበበ አራተኛ እና አምሰተኛ ለብቻቸው በቀረበባቸው ክስ ለፖሊስ ጥቆማ የሰጡ ምስክሮችን ለምን ጠቆማችሁ በሚል በማስፈራራትና በመዛት ወንጀል በመፈጸም ክስም ተመስርቶባቸዋል።

በተከሳሾቹ ላይ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ የቀረበ ሲሆን፥ ጉዳዩን የመረመረው ፍርድ ቤቱም አንደኛው ተከሳሽ በአራቱም ክስ ጥፋተኛ በማለት በሰባት አመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተቀጥተዋል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሲመራ በበኩላቸው ነፍሰጡር ሆና በማረሚያ ቤት በመውለዷ እና የስድስት ወር ህጻን በማጥባት ላይ የምትገኝ በመሆኑ በማቅለያነት ተይዞላት በአንድ አመት ከስምንት ወራትና በ1 ሺህ 200 ብር እንድትቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በታሪክ አዱኛ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram