ደቡብ ኮሪያ ከመደበኛው የስራ ሰአት በላይ የሚሰሩትን ሰራተኞች ለማስቆም ስትል ኮምፒውተሮቿን በሰዓት ልትገድብ ነው
የደቡብ ኮሪያ መንግስት በዋና ከተማ ውስጥ ያሉ ሰራተኞቻችን ሥራቸውን በሰዓቱ እንዲያቆሙ የሚያደርግ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ልታደርግ ነው።
አዲሱ አሰራር ኮምፒውተሮች በእለተ ዓርብ ልክ ከምሽቱ 3 ሰዓት ሰዓት ሲሆን በሳራቸው ስራ እንዲያቆሙ የሚያደርግ ነው።
ይህ የተደረገበት ዋናው ምክንያት የትርፍ ሰዓት ሥራ ባህል ለማስቆም ሲባል ነው ተብሏል።
ደቡብ ኮሪያ በዓለም ላይ ረዥም የሥራ ሰዓት ከሚጠቀሙ ሀገራት አንዷ ናት።
በበለፀጉ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በዓመት 1 ሺህ 739 ሰአታት የሚሰሩ ሲሆን፥ በደቡብ ኮርያ ግን የ1 ሺህ ሰዓታት ብልጫ በማሳየት በአማካይ 2 ሺህ 739 ሰዓታት ይሰራሉ ነው የተባለው።
በሴኡል ሜትሮፖሊታን አስተዳደር የታቀደው የኮምፒውተር መዝጋት መርሀ ግብር ታድያ በቀጣዮቹ ሶስት ተከታታይ ወራት ውስጥ ሶስት እርከኖችን በማለፍ ተፈፃሚ ይሆናል ነው የተባለው።
ይህም መርሃ ግብሩ በያዝነው የአውሮፓውያኑ መጋቢት 30 2018 የሚጀመር ሲሆን፥ ሁሉም ኮምፒውተሮች እለተ አርብ ላይ ከምሽቱ 4 ሰአት ይዘጋሉ።
ሁለተኛው መርሀ ግብር ደግሞ በቀጣዩ ሚያዝያ ወር የሚጀምር ሲሆን፥ በዚያው ወር በሁለተኛውና በአራተኛው አርብ ላይ የሰራተኛ ኮምፒውተሮች ከምሽቱ 3 ሰአት ከ30 ደቂቃ ይዘጋሉ።
ሶስተኛው ዙር ግንቦት ወር ላይ የሚከናወን ሲሆን፥ ከዚህ ወር ጀምሮ መርሀ ግብሩ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች ሁል ጊዜ እለተ አርብ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምረው በቋሚነት እንዲዘጉ ይደረጋል ነው የተባለው።
በዚህም ሁሉም ሰራተኞች ኮምፒውተራቸውን ለመዝጋት ይገደዳሉ፤ ሆኖም ግን ለየት ያሉ ሁኔታዎችን ሲያጋጥሙ በመርሀ ግብሩ ዙርያ በመሆን ሊታዩ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በተያያዘ ዜና የደቡብ ኮሪያ ምክር ቤት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከፍተኛውን የሥራ ሰአት በሳምንት ከ68 ወደ 52 ሰአት ዝቅ ማድረጉ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ