fbpx

የ340 ሚሊየን ግለሰቦች መረጃ በቀላሉ በሰርቨር ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ

ኤክሳይቲ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ የ340 ሚሊየን ግለሶበች መረጃ ሰዎች በቀላሉ ማግኘት በሚችሉበት ሰርቨር ላይ እንዲቀመጥ ማድረጉ ተገለፀ።

ይህ የግለሰቦች መረጃ የስልክ ቁጥር፣ የመኖሪያ ቤት፣የልጆች መጠንን እና የኢሜል አድራሻን ያካተተ መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን፥ አጋጣሚው የግለሰቦቹ መረጃ በጠላፊዎች እንዲበረበር ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በዚህ ወር ሁለት ቴራባይት መጠን ያለውና ከ100 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን ጎልማሶችና በርካታ የንግድ ሰዎች መረጃ ሳይጋለጥ አይቀርም ተብሏል።

የድህንነት ጥናት ባለሙያ የሆነው ቲሮኢያ፥ በዚህ ሁኔታ የአብዛኛው አሜሪካዊ ዜጋ ግላዊ መረጃዎች ሰዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው ተደርገው ተቀምጠው ሊሆን ይችላል ብሏል።

ባለሙያው ይህ የግለሰብ መረጃዎችን ያየዘ ስብስብ ከየት እንደመጣ ግልፅ ባይሆንም መረጃው ሰፊ ስብስቦችን የያዘ እንደሆነ ተነግሯል።

ኩባንያው በጉዳዩ ዙሪያ ምን ማረጋገጨ ባለመስጠቱ ምክንያት ምን ያህል ሰዎች ተፅዕኖ እንደደረሰባቸው ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ አልተቻለም ተብሏል።

ሆኖም የ340 ሚሊየን ሰዎችን መረጃ በሰርቨር ውስጥ እንዳለ የተገለፀ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 240 ሚሊየን የሚሆኑት የደንበኞች መረጃ እና 100 ሚሊየን የሚሆኑ የንግድ ሰዎች መረጃ ነው ተብሏል።

ይህ ኩባንያ በአጠቃላይ የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን የሚሆኑ የተጠቃሚዎች ፣ የንግድ እና የዲጂታል መረጃዎችን እንደያዘ ይነገራል።

ምንጭ፦ሲኤንኢቲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram