የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2010 ዓ.ም ሃገር አቀፍ ፈተና መውሰድ ጀመሩ።
የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።
ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።
ፈተናውን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታውቋል።
ፈተናው በመላ ሃገሪቱ በተቋቋሙ 2 ሺህ 709 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል።
የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብሄራዊ ፈተና ደግሞ ከፊታችን ሰኞ ግንቦት 27 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ይሰጣል።
ኤፍ.ቢ.ሲ
Share your thoughts on this post