የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ መከላከል የሚችል ክትባት መሰራቱ ተሰምቷል።
የብሪታኒያ ተመራማሪዎች አገኙት የተባለው ክትባቱ የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በመጨመር ካንሰሩን ለመከላከል የሚያስችል ነው።
ይህም ክትባቡ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት በሚሰጠው ተጨማሪ አቅም የፕሮስቴት ካንሰር ህዋሶች በሰውነታችን ወስጥ መፈጠር እንደጀመሩ ቀድሞ የሚገድል ነው።
ተመራማሪዎቹ ክትባቱ ገና የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ነው ቀሪ ስራዎች ይቀሩታል ብለዋል።
የቤልፋስት ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ግን ክትባቱ በእጭር ጊዜ ውስጥ ለወጣት ወንዶች መሰጠት እንደሚጀምር እና በወደፊት ህይወታቸው ለፕሮስቴት ካንሰር እንዳይጋለጡ እንደሚረዳቸው እምታቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ክትባቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተጠቁ ወንዶችን ለማከምም ይውላል የተባለ ሲሆን፥ ምክንያቱ ደግሞ ሰውነታችን ቀደም ብለው ያደጉ የካንሰሩን እጢዎች እንዲገድል አቅም ስለሚፈጥር ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk
Share your thoughts on this post