የፕሬዚዳንት ትራምፕና ኪም ጆንግ ኡን በፈረንጆቹ ሰኔ 12 በሲንጋፓር ፊትለፊት ሊገናኙ ነው

በፈረንጆቹ አቆጣጠር የፊታችን ሰኔ 12 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳን ኪም ጆን ኡን ጋር በሲንጋፖር ፊትለፊት እንደሚገናኙ ተገለጸ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቲዊተር ገፃቸው የፊታችን ሰኔ 12 ከፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን ጋር በሲንጋፖር እንደሚገናኙና በዓለም አቀፉ ሰላም ጉዳይ ላይ በመምከር የተሳካ ቆይታ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል ተብሏል።

 ሁለቱ መሪዎች እርስ በእርሳቸው ሲዎነጃጀሉ የቆዩ ቢሆንም በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለው ግንኙነቶች እየተሻሻለ ሲመጣ ፊትለፊት ተገናኝተው የመምከር ውሳኔ እውን እንዳደረገው ነው የተገገለጸው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ያሉት ቀደም ሲል በሰሜን ኮሪያ ተይዘው የነበሩ 3 የአሜሪካ ዜጎችን አቀባበል ካደረጉ ከሰዓታት በኋል መሆኑ ነው የተገለጸው።

የአሜሪካው የውጥ ጉዳይ ሚኒስተር ሚኬ ፖምፒዎ በፒያንግያንግ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ እስረኞች የተፈቱ ሲሆን፣ የሁለቱን መሪዎች ግንኙነት በተመለከተ ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቹ መሆኑም ታውቋል።

በስልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሰሜን ኮሪያ መሪ ጋር ፊት ለፊት ሲገናኝ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

ሲንጋፖር አሜሪካ ናከሰሜን ኮሪያ ጋር ወዳጅነት እንዳላት የተገለጸ ሲሆን፥ በሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እየጠናከረ ሲመጣ ከባለፈው ዓማት ህዳር ወር ጀመሮ የንግድ ግንኙነቷን አቋርጣ እንደነበረ ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram