fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የፓርኪንሰን በሽታን በትንፋሽ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ ይፋ ሆነ

ተመራማሪዎች የፓርኪንሰን የአዕምሮ በሽታን በመጀመሪያ ደረጃ በሚገኝበት ወቅት በትንፋሽ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ ይፋ ተደረገ።

ከዚህ በፊት የነበረው መሳሪያ በበሽታው የተጠቁ ሰዎችን መለየት የሚያስችለው የህክምና ክትትል ማድረግ ከጀመሩ በኋላ አንደነበረ ተነግሯል።

አሁን ይፋ የተደረገው የመመርመሪያ መሳሪያ የፓርኪንሰን በሽታ የህክምና ክትትል ሳያደርጉና በበሽታው ስር ሳይሰድ ያለበትን ደረጃ የትንፋሽ መሳሪያው መለየት ያስችላል።

ይህ የትንፋሽ መሳሪያ መመርመሪያ ጥቅም ላይ ለማዋል ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ሲሆን፥ ተመራማሪዎቹ በቀጣይ ጊዜያት ሰዎች በቀላሉ ያለባለሙያ ድጋፍ መሳሪያ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።

የፓርኪንሰን በሽታ

የፓርኪንሰን በሽታ የሰውነት አካላትና በህብረ ህዋሳት ላይ በሚፈጠር ችግር ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው።

የዚህ በሽታ ምልክቶችም፥ መንቀጥቀጥ፣ ድካም እና እራስን መቆጣጠር አለመቻል እንደሆኑ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

በሽታው ሰዎችን በሚጠቁበት ወቅት ደግሞ፥ ለድብርት፣ የማስታወስ ፣የእንቅልፍ ችግር እና የአንደበት መተሳሰር ስለሚያጋጥማቸው ለመናገር እንደሚቸገሩ በበሽታው የተደረጉ ምርምሮች ያሳያሉ።

በአለም አቀፍ ደረጃ በፓርኪንሰን በሽታ 10 ሚሊየን ሰዎች መጠቃታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

እንዲሁም በሽታው ሴቶችንም ሆነ ወንዶች የሚያጠቃ ቢሆንም በወንዶች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚስተዋል ይነገራል።

በትንፋሽ መሳሪያ ሙከራ ለማድረግ በፓርኪንሰን በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ የተባሉና የህክምና ክትትል ያልጀመሩ 29 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ በዚህም ሰዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ በሚገኘው የፓርኪንሰን በሽታ መጠቃታቸውን በተሻለ ደረጃ አሳይቷል ተብሏል።

ምንጭ፦ሜዲካልቱደይ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram