fbpx

የፌስ ቡክ የደህንነት ኃላፊ ስራውን ሊለቅ ነው

የፌስ ቡክ የደህንነት ኃላፊ አሌክስ ስታሞስ ስራውን በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚለቅ አስታወቀ፡፡
በመጋቢት ወር ፌስቡክ የደህንነቱን ጉዳይ መልሶ እንደአዲስ እንደሚያደራጅ ካሳወቀበት ወቅት ጀምሮ የአሌክስ መልቀቅ ሲጠበቅ ነበር ተብሏል፡፡

የ39 ዓመቱ አሌክስ በኃላፊነቱ ከ2015 ጀምሮ ለሦስት ዓመታት ፌስቡክን እንዳገለገለ ተገልጿል፡፡
አሌክስ ለኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ እንደገለጸው ከሆነ በፌስቡክ የሦስት ዓመታት ቆይታው እጅግ አስቸጋሪ ጊዜ ማሳለፉን ተናግሮዋል፡፡

በፌስቡክ ገጹ ደግሞ በአሁኑ ሰዕት ሁሉም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የደህንነት ስጋት የተጋረጠባቸው ወቅት መሆኑን ጠቅሶ በነበረው ቆይታም የስራ ባልደረቦቹን አመስግኗል፡፡

አሌክስ ከፌስ ቡክ ዋና ጽህፈት ቤት በ20 ኪሎሜትር ላይ የሚገኘውን ስታንፎርድ ኒቨርስቲን እንደሚቀላቀል የዓለም አቀፍ ደህንነትና ትብብር ማዕከል ተባባሪ መስራች የሆኑት ኤሚይ ዜጋርት ገልጸዋል፡፡

አሌክስ በዩኒቨርስቲውም መረጃዎች ላይ የሚሰራ አዲስ ቡድን እንደሚቀላቀል የተገለጸ ሲሆን በዚህም ለሚዲያ፣ ለፖለቲከኞችን ለሌሎችም ስጋት የተባሉ አዳዲስ መረጃዎችን መለየት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲና ሌሎች
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram