fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የፌስቡክ ባለቤት ዙከርበርግ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ይቅርታ ጠየቀ

የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎቹ መረጃ ለፖለቲካ ፍጆታ ጥቅም እንዲውል በማድረግ ማህበራዊ ድረ ገፁ ስህተት መስራቱን አመነ።

ካንብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ኩባንያ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የ50 ሚሊየን ሰዎችን የፌስቡክ ግላዊ መረጃዎች በመበርበር ለቅስቀሳ ተጠቅሟል የሚል ክስ ቀርቦበታል።

ኩባንያው መተግበሪያዎችን በመጠቀም ከፌስቡክ ላይ መረጃ ሰብስቧል የተባለ ሲሆን፥ ፌስቡክም ይህ እንዲሆን ፈቅዷል በሚል ነው ወቀሳ የቀረበበት።

በጉዳዩ ዚሪያ አስተያየት የሰጠው የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፥ “የመረጃ ምዝበራው ተከናውናል፤ ይህም ካንብሪጅ አናላይቱካ በእምነት ላይ ተመስርቶ የፈፀመው ምዝበራ ነው” ብሏል።

ይህ ተግባር እንዳሳዘነው የገለፀው ዙከርበርክ፥ ለዚህ ዓላማ የሚውሉ መተግበሪያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

“በጉዳዩ ዙሪያ የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቆሜ ማብራሪያ መስጠት ካለብኝ እና ይህ ትክክለኛ ውሳኔ ከሆነ ከሆነ በደስታ አደርገዋለው” በማለትም ተናግሯል።

ዙከርበርግ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍም፥ “ከዚህ በኋላ መተግበሪያዎች የሰዎችን መረጃ በቀላሉ እንዳያገኙ የሚሰበሰቡበትን መንገድ እናጠነክርባቸዋለን” ብሏል።

“የእናንተን መጀራ የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን፤ ይህንን ማድረግ ካቃተን እናንተን ማገልገል ለእኛ አይገባንም” ሲልም ዙከርበርግ በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

ፌስቡክ የደንበኞቹን መረጃ እያስበረበረ ነው የሚለው ክስ የቀረበበት ካንብሪጅ አናሊቲካ የተባለ ፖለቲካ አማካሪ ተቋም የ50 ሚሊየን ሰዎች የፌስቡክ አድራሻ እንደተበረበረ መገለፁን ተከትሎ ነው።

ይህ የመረጃ ብርበራ የግለሰቦችን መረጃ በፍቃዳቸው ማሰስ እንዲቻል ተደርጎ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ2013 በተዘጋጀ መተግበሪያ መከናወኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram