fbpx

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የግብዣ ጥሪ አቀረቡ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአገራቸው ብሄራዊ በዓል ላይ የክብር እንግዳቸው እንዲሆኑ ጋበዟቸው፡፡

ኢማኑኤል ማክሮን ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ታሪካዊ የሰላም ስምምነት እንዲደረስ ላደረጉት ጥረትና ላስገኙት ስኬትም እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።

ፈረንሳይ የኢትዮጵያን በዶ/ር ዐብይ አህመድ አመራር እየተመዘገበ ያለውን የለውጥ ሂደት አገራቸው በፅኑ እንደምትደግፍም ፕሬዝዳንት ማክሮን አረጋግጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በፈረንሳይ ብሄራዊ በዓል እንደሚገኙም እንደጋበዟቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ፍፁም አረጋ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ማርኮን በ30ዎቹ የዕድሜ መጨረሻ የሚገኝ የአውሮፓ ወጣት መሪ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡
በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም በተመሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የአፍሪካው ወጣት መሪ እያሉ ይገልጿቸዋል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram