fbpx
AMHARIC

የፆም ወቅት አመጋገብ የአእምሮ አቅም ማሳደግን ጨምሮ ያለው ጠቀሜታዎች

የተወሰነ ሰአት ከምግብና ከመጠጥ ዘሮች መራቅ ወይም መፆም ከሀይማኖታዊ ጥቅሙ በዘለለ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ከዚህ ቀደም የወጡ ጥናቶች አመላክተዋል።

ቢያንስ በሳምንት ውስጥ ለሁለት ቀናት መፆም ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚያመዝንም ነው ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት።

በቅርቡ የወጣ ጥናት ደግሞ መፆም የአእምሮን የመስራት አቅም ከፍ እንደሚያደርግ አሳይቷል።

ተመራማሪዎቹ ባገኙት የጥናት ውጤት ላይ ተመስርተው አንዳብራሩት፥ ሰውነታችን በፆም ወቅት ራሱን የመቋቋም ስርዓት ውስጥ ይከታል፤ ይህ ደግሞ የአእምሮን እቅም ይጨምራል ይላሉ።

ሰውነታችን በረሃብ ስሜት ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የሚፈልገውን ሀይል ከጉበት እስከ የስብ ህዋሳት ድረስ ካሉት ወደ መሰብሰብ ይዞራል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

የስብ ህዋሳት ደግሞ በውስጡ ኬቶን አለው፤ ኬቶን ደግሞ የአእምሯችንን ህዋሳት ለማበረታታት፣ የመማር አቅምን ለማሻሻል እና የአእምሯችንን የማስታወስ አቅም ለመጨመር  የሚረዳ ነው ይላሉ።

ስለዚህ ይላሉ ተመራማሪዎቹ በተከታታይ መፆም የአእምሯችን አቅም ለማሳደግ፣ የመማር እና የማስታወስ አቅምን ለመጨመር ስለሚችል ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ ብሄራዊ ጤና ኢንስቲትዩት አካል በሆነው ብሄራዊ የእድሜ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ናቸው ጥናቱን ያካሄዱት።

የእድሜ ኢንስቲትዩት የኒውሮሳይንስ ቤተ ሙከራ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ማርክ ማትሰን፥ በፆም ወቅት ሰውነታችን የሚያስፈልገውን ጉልበት በጉበት ውስጥ ከሚሰራው ከግሎኩስ እስከ የስብ ህዋስ ካሉት ያገኛል ይላሉ።

የስወነታችን ከጉበት በሚመነጨው ጉልበት መቆየት የሚችለው ከ10 እስከ 14 ሰዓት ብቻ ነው የሚሉት ማርክ ማትሰን፥ ይህ ሲያልቅ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ስብ ክምችት ይዞራል ይላሉ።

በዚህ ጊዜም ሰውነታችን ኬቶን የተባለውን ንጥረ ነገር ያገኛል፤ ይህ ደግሞ ለአእምሮ እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል ዶክተር ማርክ ማትሰን።

የጥናቱ ግኝትም ከዚህ ቀደም ጾም ከእድሜ እና ከልብ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ለመከላከል ይረዳል በሚል የተሰራውን ጥናት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።

ተጨማሪ የጾም የጤና በረከቶች

በተጨማሪም ከዚህ በፊት በተሰሩ ጥናቶች የጾም የጤና በረከቶችን መዘርዘራቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ፦

የምግብ መፈጨት ስርዓትን ለማስተካከል

የጠራ የሰውነት ቆዳ እንዲኖረን

የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ

ጥንካሬን ለማግኘት

በሽታ የመከላከል አቅምን ለመጨመር እንደሚረዳ ተመልክቷል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk/health

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram