fbpx

የፀጉር መነቀል ችግርን ለመከላከል ….

የፀጉር መነቀል የአብዛኛው ሰው ችግር ሲሆን፥ ፆታን ሳይለይ የወንድንም ሆነ የሴቶን ተፈጥሮ ፀጉር እየተመናመነ እንዲሄድ የሚያደርግ ችግር ነው።


ችግሩ ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻርና ፀጉር የነበራቸው ሰዎች በሂደት እየቀነሰ በመሄድ የእራስን ውበት የሚያጠፋና በአንዳንድ ሰዎች ላይ ጭንቀትን የሚፈጥር እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ ለአብዛኛው ሰው ችግር የሆነው እና በርካቶች መፍትሄ የሚፈልጉት ጉዳይ ለሆነው የፀጉር መነቀል ችግር የተወሰኑ መፍትሄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
1. አመጋገብን ማስተካከል

የፀጉር መነቀልን ለመከላከል ከሚያስችሉ ጉዳዮች መካከል የአመጋገብ ስርዓትን ማስተካከል የሚጠቀስ ሲሆን፥ በፕሮቲንን የበለፀገ ምግብ ማዘውተር ያስፈልጋል።

ፕሮቲን በሰውነት ውስጥ የህዋሳት እንዲያድጉ የሚያደርገ ሲሆን፥ ይህም ፀጉርን ያካተተ እንደሆነ ይነገራል።

በመሆኑም በየዕለቱ በቂ ፕሮቲን ያላቸው ምግቦችን መመገብ ያስፈልጋል። ፕሮቲንን በበቂ ሁኔታ ከያዙ ምግቦች መካከል ወተት፣ እንቁላል እና አሳ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

ከዚህ ባለፈ በሳምንት ለሁለትና ሶስት ጊዜያት ከፍተኛ መጠን የኦሜጋ 3 ያለበት ምግብ መመገብ ያስፈልጋል።

2. ቫይታሚን ማዘውተር

በእየለቱ በቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ፀጉር ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የሚነገረው።

እንቁላል፣ ካሮት እና የአትክልት ምግቦችን መመገብ በቀላሉ ቫይታሚን ኤን ማግኘት ያስችላል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ቫይታሚን ቢ12 ቀይ የደም ህዋስን በመፍጠር እና ቫይታሚን ኢ ደግሞ ለሰውነት በቂ ኦክስጂን በማቅረብ ጤናማ የሆነ ዝውውር እንዲኖርና ፀጉርም በቂ ኦክስጂን እንዲያገኝ ያስችላሉ።
ለጤና ፀጉር አስፈላጊ ከሆኑ ማዕድናት መካከል ካልሽየም፣ ኮፐር፣ ብረት ማግኖዥየም እና ዚንክ ይጠቀሳሉ።

3. የህክምና ክትትል ማድረግ

ሰዎች ፀጉራቸው በፍጥነት እየተነቀለ የሚሄደው የሆርሞን አለመመጣጠን በሚኖርበት ወቅት ነው።

በመሆኑም ሰዎች ይህን የሆርሞን አለመመጣጠን ሲያጋጥማቸው የህክምና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ የሆርሞን አለመመጣጠኑን ሊያስተካክሉ የሚችሉ እና ጤናማ የሆርሞን እድገት እንዲኖር የሚያስችሉ ምግቦችን መመገብ ያስፈልጋል ተብሏል።

4. አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶችን ማቆም

ሰዎች የተለያዩ አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶችን በህይወታቸው ተግባራዊ ያደርጋሉ ይህም ከፍተኛ የጤና ችግርን እንደሚፈጥር ይታወቃል።

ከእነዚህም ውስጥ ሲጃራ ማጨስ ይጠቀሳል፥ ሲጃራ በሰውነት ውስጥ የደም እና ሌሎች ዝውውር ስራዓቶች እንደሚያዛባ ይገለፃል።

አልኮል ደግሞ በሽታ የመከላከል ችግርና እና ፀጉር እንዲነቀል ምክንያት እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን፥ እነዚህን አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶችን በማቆም የፀጉር ጤናን መጠበቅ ይቻላል።

5. የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖር ማድረግ

አብዛኛውን ጊዜ ጭንቀት እና ውጥረት ለፀጉር መነቀል ምክንያት እንደሆነ ይነገራል በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍና አዕምሮን ለማረጋጋት ተመስጦንና ዮጋን መልመድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

6. የአካል እንቅስቃሴ

የአካል እንቅስቃሴን ማድረግ በፀጉር ውስጥ የሚገኙ ተህዋሲያን ለማስወገድ የሚረዳ ሲሆን፥ ፀጉር በተሻለ ሁኔታ እንዲያድግና ጠንካራ እንዲሆንም ያስችሏል።
ከላይ ከተጠሱት ጉዳዮች በተጨማሪ አስፈላጊ የፀጉር ዘይት፣ ተፈጥሮአዊ ጁስ፣ አረንጓዴ ሻይ በመጠቀም እና ፀጉርን በስርዓቱና በአግባቡ መከባከብም ለጤናማ ፀጉር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ዋንጉድ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram