fbpx

የጸጉር መዋቢያዎች በጥቁር አሜሪካዊ ሴቶች ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ አንድ ጥናት አመለከተ

ጥቁር አሜሪካዊ ሴቶች በብዛት የሚጠቀሟቸው የጸጉር መዋቢያዎች በውስጣቸው የሚይዟቸውቅ ንጥረ ቅመመሞች/ ኬሚካሎች/ ጤናን ሊጎዱ እንደሚችሉ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

የጥናቱ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ጀሲካ ሄልሜና ሌሎች የጥናቱ ተሳታፊዎች በ18 ጥቁር አሜሪካዊያን ሴቶች በሚጠቀማችው የጸጉር መዋቢያዎች ላይ ባደረጉት ጥናት መዋቢያዎቹ በሰዎች ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ንጥረ ቅመም ይዘት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

የጸጉር መዋቢያዎቹ የንጥረ ቅመም ይዘታቸው ላይ ቁጥጥር እና ምርመራ የማይደረግባቸው መሆኑንም ነው የጥናቱ ጸሃፊ የተናገሩት።

በመዋቢያዎች ውስጥ የተገኙት ንጥረ ቅመሞች በሰዎች ሰውነት ውስጥ ጠቃሚ የሰውነት ንጥረ ቅመም በሚያመነጩ እጢዎች ላይ የጤና ጉድለት እንደሚያስከትሉ ነው ተመራማሪዎቹ ያረጋገጡት።

ቀደም ባሉት ጥናት ግን የእነዚህ ንጥረ ቅመም አመንጪ እጢዎች ላይ የሚከሰተው የጤና እንከን ከካንሰር፣ ከጽንስና ከጽንስ ጋር ከተያያዙ ችግሮች እና ከመተንፈሻ አካላት ህመምች ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ናቸው ተብሎ ይታወቅ የነበረ መሆኑን ነው የተገለጸው።

ጥናቱ በተደረገባቸው የጸጉር መዋቢያዎች ውስጥም በአውሮፓ ህብረት አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ከተከለከሉ ንጥረ ቅመሞች መካከል 7 መገኘታቸውን መረጃው አመላክቷል።

በዚህም ጥቁር አሜሪካዊ እናቶች ከሚጠበቀው ጊዜ ቀድመው ለአቅመ ሄዋን መድረስ፣ ለጽንስ መቋረጥ፣ ለመሃንነት፣ ለጡትና መሃጸን ካንሰር ሊያጋልጡ የቻሉ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመላከተው።

ረዳት የጥናቱ ጸሀፊ ሮቢን ዶድሰን በበኩላቸው አንዳንድ የማዋቢያ አምራች ኩባንያዎችም በመዋቢያዎቹ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ቅመሞችን ለደንበኞቹ ግልጽ ያለማድረጋቸውን ነው የገለጹት።

ጥናቱ የጥቁር አሜሪካዊ እናቶች በመዋቢያዎች ሳቢያ በጤናቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በማመላከት ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል ነውም ተብሏል።

 

ምንጭ፦ upi.com

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram